Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ በህዳሴ ግድብ ላይ ለሚካሄደው የሶስትዮሽ ውይይት ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ  

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚካሄደው የሶስትዮሽ ውይይት ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ።

ከዚህ ቀደም ሀገራቱ በደረሱት ስምምነት መሰረት ነው ነገ  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በዋሽንግተን የሚገናኙት።

በውይይቱ የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ይሳተፋሉ።

በነገው ውይይትም ሀገራቱ በተለያዩ ዙሮች የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያደረጓቸውን ድርድሮች ውጤት ይመለከታሉ።

በዚህ ውይይታቸውም አሜሪካ እና ዓለም ባንክ በታዛቢነት ይሳተፋሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.