Fana: At a Speed of Life!

“አንድነት ለኢትዮጵያ” የቴሌግራም ግሩፕ ጉዳት ለደረሰባቸው የሰራዊት አባላት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድነት ለኢትዮጵያ የቴሌግራም ግሩፕ በህልውና ዘመቻው ጉዳት ለደረሰባቸው የሰራዊት አባላት የአልባሳትና የአይነት ድጋፍ አደረገ።

የቴሌግራም ግሩፑ በአገር ወስጥና በውጭ የሚኖሩ አገር ወዳድ ዜጎችን ያሰባሰበ ሲሆን ÷ በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሱ ያልተገቡ ጫናዎችን በመቃወምና እውነታዎችን ለዓለም ማህበረሰብ በማሳወቅ ይሰራል።

በዛሬው እለት ደግሞ ለአገር ህልውና ሲፋለሙ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ለሚገኙ የሰራዊት አባላት ድጋፍ አድርጓል።

በአሜሪካ የሚኖሩት የአንድነት ለኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ህብተወልድ ግሩፑ የኢትዮጵያን አውነታ ለዓለም ማህበረሰብ በማሳወቅ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ÷ በዛሬው እለት ደግሞ ለጀግኖች የሰራዊቱ አባላት ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

የዛሬው ድጋፍም በውጭ ሀገር ከሚኖሩ የአንድነት ለኢትዮጵያ አባለት በተሰባሰበ ገንዘብ የተለያዩ አልባሳትና የንጽህና መጠመበቂያ ቁሳቁስ የተለገሰ መሆኑን ገልጸዋል።

ለአገር ሉአላዊነት ለሚዋደቁ ጀግኖች ይህን ማድረግ ለሀገር ማድረግ ከሚገባን በጣም ትንሹ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

አሁን ኢትዮጵያ የገጠማት ፈተና እንደ አድዋ ሁሉ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ታሪክ ሰርተው የሚያለፉበት ልዩ አጋጣሚ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ከአንድነት ለኢትዮጵያ የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት የጦር ሃይሎች አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማኔጅመንት አባል ኮሎኔል ዘለቀ ደሪሳ ÷ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

ማህበረሰቡ በራሱ ተነሳሽነት ለአገር መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለው ድጋፍ ትልቅ የሞራል ስንቅ በመሆኑ ተጠናክሮ እነዲቀጥል መጠየቃቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.