Fana: At a Speed of Life!

አክሲዮን ማህበሩ ለማህበረሰብ አገልግሎት እያደረገ ያለው አስተዋፅዖ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ናሽናል ሲሚንት አክሲዮን ማህበር ግምታቸው 1 ሚሊየን የሆኑ የኦክስጅን ሲሊንደርና የተለያዩ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ለድሬዳዋ ጤና ቢሮ አበርክቷል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር አክሲዮን ማህበሩ በማህበረሰብ አገልግሎት እያበረከተው የሚገኘው አበርክቶ የላቀ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
የአስተዳደሩ የጤና ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ለምለም ማህበሩ በተለይም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር በከተማዋ በተበራከተበት ጊዜ ፋብሪካው የግል መገልነያ የሆኑት የኦክስጅን ሲሊንደሮች በዉሰት ሰጥቶ እንደነበር አስታውሰዋል።
አያይዘውም አሁን በስጦታ የተበረከቱት የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶቹ በዘርፉ የሚታዩትን ክፍተቶች ለመሙላት ያግዛል ብለዋል።
የፋብሪካ የዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ አዳነ አለሙ በበኩላቸው ÷ፋብሪካው በማህበረሰብ ተሳትፎ የበኩልን እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰው የዛሬው ድጋፍም የዚሁ አንድ አካል መሆኑን አስታውቀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በስጦታ ከተሰጡት 1መቶ ሲሊንደሮች መካከል ለሃያው በየሳምንቱ ፋብሪካው የኦክስጅን ሙሌት እንደሚያከናውን ገልጸዋል።
በእዮናዳብ አንዷለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.