Fana: At a Speed of Life!

አዋሽ ባንክ “ታታሪዎቹ” የተሰኘ 1 ሚሊየን ብር ሽልማት የሚያስገኝ የሥራ ፈጠራ ውድድር ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ ባንክ “ታታሪዎቹ” የተሰኘ የሥራ ፈጠራን በማበረታታት የሥራ አጥነት ችግርን ሊፈታ የሚችል ውድድር ይፋ አድርጓል::

ፕሮጀክቱ ሥራ ፈጠራን ከማበረታታት ባሻገር ክህሎት ላላቸው ሥራ ፈጣሪዎች የቢዝነስ ሙያ ሥልጠና እና የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል፡፡

“ታታሪዎቹ” የተሰኘው የሥራ ፈጠራ ውድድር 1 ሺህ ተወዳዳሪዎችን የሚያሳትፍ ሲሆን ÷ተወዳዳሪዎቹ ፕሮጀክቱን በአማርኛ ፣አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች ማቅረብ እንደሚችሉም ተመላክቷል፡፡

የውድድሩ አሸናፊ የሥራ ፕሮጀክቱን አሻሽሎ በማቅረብ ወደ ሥራ እንዲገባ ሚያስችለው የአንድ ሚሊየን ብር ሽልማት እንደሚያገኝ ባንኩ አስታውቋል፡፡

በማስጀመርያ መረሐ ግብሩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የባንኩ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ባንኩ ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ተቀናጅቶ የሥራ ፊጠራን ለማበረታታት እደሚሠራ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጸሀይ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡

በዱሬቲ ቶሎሳ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.