Fana: At a Speed of Life!

አው አባድር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በቀጣይ ዓመት ሥራ እንደሚጀምር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በ2015 የበጀት ዓመት አው አባድር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ግንባታ ሥራ አጠናቆ አገልግሎት ለማስጀመር በትኩረት እንደሚሰራ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተገነባ የሚገኘውን የአው አባድር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን የግንባታ ሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

በዚዙ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት÷ የክልሉ መንግስት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅና ስራ ማስጀመር እንዲሁም የሚጀመሩ አዳዲስ ፕሮጀክቶችንም በታቀደላቸው የጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ ነው።

ከዚህም ውስጥ የአው አባድር አለም አቀፍ ስታዲየምን የመጀመሪያ ምዕራፍ ማጠናቀቅና ስራ ማስጀመር አንዱ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ጠቁመው÷ ለዚህም በጀት መመደቡን ገልጸዋል።

የስታዲየሙ መጠናቀቅ ክልሉን በስፖርት የቱሪዝም ማዕከል እንዲሆን እንደሚያስችል የገለጹት አቶ ኦርዲን በድሪ÷ የስታዲየሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ የግንባታ ደረጃ 95 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ፣ አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.