Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ “ሴበር” ከተሰኘው ቀዳሚ የሶፍት ዌርና ቴክኖሎጂ አቅራቢ ኮርፖሬሽን ጋር የነበረውን የሥራ ስምምነት አደሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሴበር  ጋር የገባውን ለረጅም ጊዜ ያቆየ ስትራቴጂካያዊ ሽርክናው ያደሰው ለቀጣይ ሰባት ዓመታት ቢያንስ የ110 ሚሊየን ዶላር አገልግሎት ለመግዛት ውል ገብቶ ነው፡፡

በሥምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ‘‘ሳብሬ”ን የመንገደኞች አገልግሎት ሥርዓት መጠቀም እንደሚቀጥል ተመላክቷል፡፡

በስምምነቱ አየር መንገዱ ÷ የሽያጭና የደንበኞች አገልግሎቱን የሚያቀላጥፍ፣ የገቢ ማሳደጊያ ዕድሎችን የሚፈጥር እንዲሁም ለመንገደኞች ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ሴበር  ሶኒክን የተሰኘውን አገልግሎት መጠቀም ይቀጥላል ተብሏል፡፡

በአየር መንገዱ ከሴበር ኮርፖሬሽን በሚቀርብለት የ“Sabre’s Intelligence Exchange” የመረጃ ልውውጥ ለመንገደኞቹ ተደራሽ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

የሴበር  ኮርፖሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ዲኖ ጌልመቲ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተጽዕኖ ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቬሽን ኢንዱስትሪው ስኬታማ ሆኖ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡

በአንጻሩ ወረርሽኙ የአየር መንገዶችን ተወዳዳሪነትና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፍላጎትን እያፋጠነ ሲሆን÷ የአፍሪካ አቬዬሽን ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድም ተለዋዋጭ እየሆነ ከመጣው ዓለም ጋር እራሱን እያመቻቸ ፣ አገልግሎቱን እያሻሻለ ነውም ብለዋል፡፡

የታደሰው ስምምነት አየር መንገዱ በገበያ ፍላጎትና ውድድር ላይ የተመሠረተ የዋጋ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ምክረ ሃሳቦችን በማቅረብ ተወዳዳሪና ተጠቃሚነቱን እንደሚያሳድግ አስታወቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ጠንካራ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መኖሩ ለስኬታችን ቁልፍ ሚና ይጫወታል ያሉ ሲሆን÷የሴበር የደህንነት ቴክኖሎጂም አየር መንገዱ ከአዲሱ የዓለም ገጽታ ጋር በፍጥነት ለመላመድ ይረዳዋል ነው ያሉት፡፡

የጉዞ ኢንደስትሪው ማገገም ሲጀምርም በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋና ዘመናዊ ተግባራትን በማከናወን ትርፋማነትና እድገት ላይ ያተኮሩ ወሳኝ ሥራዎችን ለመሥራት ያስችላል ብለዋል፡፡

የሴበር  ጠንካራ የጉዞ መድረክ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መፍትሄዎች አየር መንገዶች ፣ ኤጀንሲዎች እና ሆቴሎች የሚመኩበትን ቴክኖሎጂን እንደሚሰጡ ኤር 101 አስነብቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.