Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ወደ ቤንጋሉሩ ከተማ ቀጥታ በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቤንጋሉሩ ከተማ ቀጥታ በረራ መጀመሩን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት የቴክኖሎጂ ማዕከል ወደ ሆነችው የደቡቧ ህንድ ከተማ ቤንጋሉሩ ቀጥታ በረራ መጀመሩን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎም ቤንጋሉሩ አየር መንገዱ ወደ ህንድ በሚያደርገው በረራ ከዴልሒ እና ሙምባይ ቀጥላ ሶስተኛ የህንድ መዳረሻ ከተማ ሆናለች።

በረራው በአሁኑ ወቅት በሳምንት ለአራት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፥በቀጣይ ወደ ከተማዋ የሚደረገውን በረራ በየቀኑ ለማድረግ መታሰቡንም ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.