Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ የሲኤንኤን ዘገባ ሀሰተኛ ነው ሲል ዘገባውን ተቃወመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጦር መሣሪያዎችን ማጓጓዝን አስመልክቶ በሲኤንኤን የቀረበውን ዘገባ ሀሰተኛ መረጃ ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአይ ኤ ቲኤን ከፍተኛ አባል እና የስታር አሊያንስ አባል በመሆን ለአፍሪካና ለተቀረው የአለም ሃገራት አስተማማኝና ምቹ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
አየር መንገዱ ላለፉት 75 ዓመታት በመልካም እና በመጥፎ ጊዜያት ሁሉንም ብሔራዊ፣ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ተዛማጅ ደንቦችን በጥብቅ በማክበር በአገልግሎቱ ተቀዳሚ እና የተመሰገነ አለማቀፍ ተቋም መሆኑም በመግለጫው ተወስቷል፡፡
አየር መንገዱ የጦር መሳሪያና ሌሎች ያልተፈቀዱ እቃዎችን አጓጉዟል በሚል ሲ ኤን ኤን ያሰራጨዉ ውንጀላ መሰረተ ቢስ መሆኑን ጠቅሶ በዘገባዉ ያካተታቸዉ እቃዎችን አየር መንገዱ አያቃቸውም ብሏል በመግለጫው፡፡
እቃዎች የሚጓጓዙት በ አይ ኤ ቲኤን ደረጃዎች መሠረት ተፈትሸዉ ሲሆን ÷ እንዲሁም በብሔሩ ምክንያት የታገደ ወይም የተባረረ ሰራተኛ አለመኖሩን እና ይህንንም ከሰው ሀብቶቻችን መዛግብት ሊረጋገጥ ይችላል ሲል ውንጀላዉን ውድቅ በማድረግ ሚዲያዉ እርማት እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡
አየር መንገዱን በአፍሪካ ውስጥ ቀዳሚ አየር መንገድ አድርጎ ያስቀመጠው ባለፉት አስርት ዓመታት በሁሉም መለኪያዎች ካስመዘገበው ፈጣን ዕድገት መሆኑን ጠቅሶ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮሮና ወረርሽኝ ቀውስ በመቆጣጠር ረገድ፤ በፈጠራ ስራዉ እና የውሳኔ አሰጣጥ ስራዉም ዉጤታማና ስኬታማ እንደነበር መግለጫዉ ጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁሉንም ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ተዛማጅ ደንቦችን እና መስፈርቶችን በጥብቅ የሚያከብር፣በሁሉም የሥራ ክንውኖች ውስጥ የሲቪል አቪዬሽን ደንቦች ተከትሎ የሚሰራ፣ በማንኛውም የጦር መሣሪያ መጓጓዝ ውስጥ ተሰማርቶ የማያውቅ መሆኑን ለሁሉም ተሳፋሪዎቻችን እና ለህዝቡ እናረጋግጣለን ማለቱን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.