Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ የዓለም አቀፍ አየር መንገድ የጭነት ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት የአመቱ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ የጭነት ሽልማትን አሸነፈ።

ዓለም አቀፍ ሽልማቱን ያሸነፈው በህንድ ሙምባይ በተካሄደ ስነ ስርዓት ነው ተብሏል።

አየር መንገዱ የጭነት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጭነት ኢንዱስትሪው በፍጥነት እንዲያድግና ተወዳዳሪ እንዲሆን ባደረገው አስተዋፅኦ ሽልማቱን ማሸነፉም ነው የተነገረው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ ሽልማቱ አየር መንገዱ በሚያከናውናቸው ስራዎች የበለጠ እንዲነሳሳ ያስችለዋል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም አየር መንገዱ በአፍሪካ ብሎም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሚሰጠው የጭነት እና የሎጅስቲክስ አገልግሎት ለመሪነቱ ማረጋገጫ መሆኑንም ተናግረዋል።

አየር መንገዱ አገልግሎቱን በቀጣይነት ለማስፋፋት እና ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝና ተወዳዳሪ የጭነት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስራ መስራቱን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.