Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ 95 ሚሊየን የአበባ ዝንጣፊ ለተለያዩ ሀገራት ማጓጓዙን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 95 ሚሊየን የአበባ ዝንጣፊ ለተለያዩ ሀገራት ማጓጓዙን ገለፀ፡፡
 
አየር መንገዱ 95 ሚሊየን የአበባ ግንጣይ ወይም ዝንጣፊውን ማጓጓዝ የቻለው በቫላንታይን ወቅት ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡
 
የአየር መንገዱ ካርጎና ሎጀስቲክስ አገልግሎት እንዳታወቀው ከተጓጓዘው አበባ 1 ሺህ 600 ቶን ከናይሮቢ ሲሆን 3 ሺህ ቶን ደግሞ ከአዲስ አበባ ነው፡፡
 
የአበባ ምርቱም ወደ ቤልጂየም፣ ኮትዲቯር፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ፣ አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓጉዟል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.