Fana: At a Speed of Life!

አይ ኤም ኤፍ ለማይናማር የ356 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ለማይናማር የ356 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ አጸደቀ።

የገንዘብ ድጋፉ ሃገሪቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የገባችበትን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለማገዝ የሚውል ነው ተብሏል።

ተቋሙ ሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ከቱሪዝም ዘርፍ የምታገኘው ገቢ እንዲሁም ከዜጎች ከሚላክ ገንዘብ የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን አስታውቋል።

ይህን ተከትሎም ድጋፉ መደረጉን ነው ያስታወቀው።

አሁን የተደረገው ድጋፍ በሃገሪቱ አስቸኳይ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን ዘርፎች በመለየት ለማጠናከር ይውላል ነው የተባለው።

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.