Fana: At a Speed of Life!

አደገኛ ዕፆች አጠቃቀም እና መከላከል ፖሊሲ አፈጻጸም ላይ የሚመክር አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ በመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የስብሰባ ማዕከል ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ የአደገኛ ዕፆች አጠቃቀም እና መከላከል ፖሊሲ አፈጻጸም ላይ የሚመክር አውደ ጥናት እየተካሄደ ይገኛል።

አውደ ጥናቱ የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አደገኛ ዕፆችና ወንጀሎች መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት በጋራ ያዘጋጁት ነው።

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሊያ ከበደ፥ የአደገኛ ዕፆችን ዝውውርና ወንጀልን ለመከላከል የዓለም እና ሃገር አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጥምረት ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በበኩላቸው፥ ባለስልጣኑ አደገኛ ዕፆችን ለመቆጣጠርና የዜጎችን ጤንነት ለመጠበቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።

በአውደ ጥናቱ ላይ ከ40 በላይ ሃገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ሲሆን፥ ተሞክሮዎችና ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

አደገኛ ዕፆችን ለመቆጣጠር ሀገር አቀፍ ፖሊሲና ስትራቴጂ ለማዘጋጀት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የቴክኒክ ቡድን እንደሚዋቀር መገለጹን ከኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.