Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ መንግስት ሌብነትን ለመቆጣጣር ከአገልግሎት አሰጣጥ እስከ ባለስልጣናት የተዘረጋውን መረብ መበጣጠስ አለበት- ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የመንግስት አስተዳደር ስር የሰደደውን ሌብነት ለመቆጣጣር ከመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ባለስልጣን ድረስ የተዘረጋውን መረብ ቅድሚያ ሰጥቶ መበጣጠስ ይገባል አሉ የህግ እና የጸረ ሙስና የማህበረሰብ አንቂ ምሁራን።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የጸረ ሙስና የማህበረሰብ አንቂና የህግ አማካሪው አቶ ክብረ አብ አበራ÷ በመንግስተ ባለስልጣናት ደባ በሚፈጸም ሌብነት ሀገር ሀብቷ ተዘርፏል።
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህሩ አቶ ሀይሉ ነጋ÷ ከግዙፉ ስርቆት እስከ አገልግሎት አሰጣጥ በደል የደረሰው የሌብነት ተግባር እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።
በመንግስት ስራ ተቀጥሮ ደመወዝ የሚከፈለው ሰራተኛ ጭምር በዚሁ የሀገር ሀብት ስርቆት ውስጥ እጁ ቆሽሿልም ብለዋል።
በሁሉም ዘርፎች የተንሰራፋው ስርቆት በአዲሱ ምእራፍ ወደ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገቱ እንዳይደናቀፍም የምዝበራ ሰንሰለቱን ለመቆጣጠር መስራት አለበት ነው ያሉት ምሁራኑ።
በኃይለየሱስ መኮንን
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.