Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ ዓመት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ወደ ተመኘው ሲኦል የሚመለስበት ይሆናል – ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “አዲሱ ዓመት አገር ለማፍረስ ተላላኪ ሆኖ የመጣውን የህወሓት ቡድን ወደተመኘው ሲኦል በመመለስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ጠንክረን የምንሰራበት ይሆናል” ሲሉ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ተናገሩ።
በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ 2013 የውስጥና የውጭ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የፈተኑን ጊዜ እንደነበር አውስተዋል።
ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊና ዲፕሎማሲያዊ አንድነቷ ተጠብቆ እንዳትቀጥል የሚሹ አፍራሽ ኃይሎች በከፈቱት ጦርነት በሰውና በንብረት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳትም ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በኃይማኖት፣ በሃብትና በዕድሜ ሳይከፋፈሉ አገራቸውን ሊያፈርስ የመጣውን ኃይል ለመመከት በአንድነት ቆመዋል ብለዋል።
ባለሀብቱ ለሃብቱ ሳይሰስት፣ አርሶ አደሩ፣ የከተማ ነዋሪውና ነጋዴው ያለውን በማዋጣት የትም፣ መቼም፣ በምንም ለአገሩ ሉዓላዊነት መዝመት እንደሚችል በተግባር የሚያሳይበት የታሪክ አጋጣሚ መፈጠሩንም ተናግረዋል።
ይህ አንድነት ለውስጥና ለውጭ ጠላቶች በተለይም በልዩነት ላይ ሲሰራ ለኖረው ለአሸባሪው ቡድን ኢትዮጵያን የማፍረስ ሕልም “ውሃ እንደበላው ተረጋግጧል” ነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ።
የተጠናቀቀው ዓመት ኢትዮጵያዊያን ቋንቋ፣ ብሔር፣ ኃይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከት ሳይገድባቸውአገራቸውን አሳልፈው እንደማይሰጡ ያስመሰከሩበት ዓመት በመሆኑ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አዲሱ 2014 ዓ.ም አገር ለማፍረስ ተላላኪ ሆኖ የመጣውን የጁንታውን ቡድን ወደመጣበትና ወደ ተመኘው ሲኦል በመመለስ ኢትዮጵያ ሉዓላዊት አገር እንድትሆን ጠንክረን የምንሰራበት ነው ሲሉም አክለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.