Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ቁጥጥር እየተደረገ ነው – የጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የተገኘው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ÷ የኮቪድ 19 ስርጭት መቆጣጠር አለመቻሉ አዳዲስ ዝርያ እንዲመጣ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
ይህም ቫይረሱን በቶሎ ለመቆጣጠር የሚደረገውን ስራ ፈታኝ አድርጎታል ነው ያሉት።

 

አዲስ የኮቪድ 19  ዝርያ  በመምጣቱ  በርካታ የአለም ሃገራት በወረርሽኝ እየተመቱ በመሆኑ  ክትባቱን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ያሳሰቡት ሚኒስትሯ  ÷ ባለፉት ሁለት ሳምንት እየተሰጠ በሚገኘው የክትባት ዘመቻ  እስካሁን ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የክትባት ዶዝ መስጠት ተችሏል   ብለዋል፡፡

አዲስ የኮቪድ 19  ዝርያ የሆነውን “የኦሚክሮን” ቫይረስ ለመከላከል በመግቢያ በሮችና በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የነበሩ ቁጥጥሮችን  የማጥበቅ ስራ እየተሰራ  መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን ከ6 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል።

 

 

 

በሃይማኖት ኢያሱና በከድር መሃመድ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.