Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ሁላችንንም የምታሰባስብና የምታፋቅር ናት – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ1 ሚሊየን በላይ የብልጽግና ደጋፊዎችና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡

ፕሮግራሙን አስመልክተ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ “ዛሬ ከ 1 ሚሊየን በላይ የፓርቲያችን የብልጽግና ደጋፊዎችና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ እና ለደጋፊዎቻችን ምስጋና አቅርበናል” ብለዋል ።

በአዲስ አበባ ማንም ተወላጅና መጤ ተብሎ እንደማይከፋፈል፣ አዲስ አበባ ሁሉንም የምታሰባስብና የምታፋቅር እንጂ የምታጣላ አለመሆኗን እንዲሁም በቂ ሃብት እንዳላትና ይህን ከቀማኞችና ሌቦች መታደግ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያን መፃኢ እጣ ፈንታዋን የሚወስነው ወሳኙ ምዕራፍ ላይ መደረሱን ያነሱት ምክትል ከንቲባዋ፥ ምርጫውን ሰላማዊና ዴምክራሲያዊ በማድረግ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ሃገር ከምርጫና ከየትኛውም ፓርቲ በላይ ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች፥ “ተፎካካሪ ፓርቲዎች ልዩነት የፖለቲካ አስተሳሰብ መሆኑን በመገንዘብ ወንድምና እህት መሆናችንን በታላቅ ድምፅ አሰምተናል” ብለዋል ።

መራጮች በምርጫው በአንድ እጅ ካርድ በሌላኛው እጅ ሃገር በቀል ችግኝ በመያዝ ኢትዮጵያን እናልብስ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፤ ኢትዮጵያን በተመለከተ ለመላው ዓለም አዲስ አስተሳሰብና አመለካከት መፍጠር እንደሚገባ በመጥቀስ።

የከተማዋ ነዋሪዎች በምርጫው ቅስቀሳ ወቅት መንገድ ሲዘጋና በጨዋነትና በአርቆ አሳቢነት ላሳዩት ትዕግስትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.