Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኮሮና ቫይረስ ላይ ጥናት ለማካሄድ 10 ሚሊየን ብር መደበ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ )አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19 )ላይ ጥናት ለማካሄድ 10 ሚሊየን ብር መመደቡን አስታውቋል።

በዛሬው እለት በኮቪድ-19 ላይ ጥናት የሚያኪያሂድ የጥናት ቡድን የተቋቋመ ሲሆን ፥ቡድኑ ጥናቱን ለመጀመር ከተመደበው አጠቃላይ ፈንድ ውስጥ አንድ ሚሊየን ብር ወጪ ሆኖ ተሰጥቶታል።

ለጥናቱ የተመደበው ቀሪው ገንዘብ በውድድር ላይ ተመስርቶ በመሰል ጥናት ለመሳተፍ ለሚሹ የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ስታፍ አባላት የሚቀርብ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የጥናት ቡድኑ አባላት ከተለያዩ ኮሌጆችና ተቋማት ከልዩ ልዩ መስክ የተውጣጡ ምሁራንን ያካተተ ሲሆን፥ የመጀመሪያ ስብሰባውንም በዛሬው ዕለት አድርጓል።

የጥናት ቡድኑ የኮሮና ቫይረስ ለመዋጋት ለሚደረገው ጥረት አስተዋፅኦ ለማድረግ ጠቃሚ ግብዓት ሊሆን የሚችል የጥናት ግኝቶችን እንደሚያቀርብ ታምኖበታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.