Fana: At a Speed of Life!

አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያላቸውን ቅሬታ ከዛሬ ጀምሮ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፤ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአመዳደብ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ከዛሬ ጀምሮ ማቅረብ እንደሚችሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በአካል ቅሬታ የሚያቀርቡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ገልጿል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ምደባ ሚያዚያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

በዚሁ መሰረት የተመደቡ ተማሪዎች በአመዳደብ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ከሚያዚያ 25 እስከ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ማቅረብ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው በሚኒስቴሩ ድረ ገጽ፣ የኢ-ሜይል እና በስልክ አድራሻዎች ማቅረብ እንደሚችሉ አመልክቷል።

ተማሪዎች በድረ-ገጽ https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7፣ በስልክ ቁጥር +251911763794 እና +251943543805 እንዲሁም የኢ-ሜይል አድራሻ support@ethernet.edu.et ቅሬታ የሚያቀርቡባቸው አማራጮች መሆናቸው ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ በአካል ቅሬታ የሚያቀርቡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.