Fana: At a Speed of Life!

አዲሷ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ካቢኔያቸውን በአዲስ መልክ አዋቀሩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊን ህልፈት ተከትሎ አዲሷ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት የሆኑት ሳሚያ ሱሁሉ  አዲስ የሚኒስትሮች ካቢኔን አዋቅረዋል።

ፕሬዚዳንቷ ባዋቀሩት አዲስ የሚኒስትሮች ካቢኔ ውስጥ አዳዲስ ሰዎች መካተታቸው ተገልጿል።

ከእነዚህ ውስጥ ዲፕሎማቷ ሊበራታ ሙላሙላ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ተሾመዋል።

ሊበራታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉትንና አሁን ወደ ቀድሞ የፍትህ እና የሕገ-መንግስታዊ ጉዳዮች ቢሮ የተመለሱትን ፕሮፌሰር ፓልማጋምባ ካቡዲን በመተካት ነው ተብሏል ፡፡

ሊበራታ ሙላሙላ  በአሜሪካ የታንዛኒያ አምባሳደር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን አሁን የያዙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታም በፈረንጆቹ 2006 እና 2007 ካገለገሉት  ከዶክተር አሻ-ሮዝ ሚጊሮ በመቀጠል  በሀገሪቱ ታሪክ ሁለተኛዋ ሴት ያደርጋቸዋል።

ፕሬዚዳንቷ ዶክተር ፊሊፕ ምፓንጎን በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሰይመዋል፡፡

ምንጭ ፡-ቢቢሲ

የፊታችን አርብ ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.