Fana: At a Speed of Life!

አዲሷ የአሜሪካ አምባሳደር የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጅ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን ጊታ ፓዝን የሹመት ደብዳቤ ቅጅ ተቀበሉ፡፡

አምባሳደር ሬድዋን አሜሪካ የኢትዮጵያ ረጅም ጊዜ ወዳጅ ሃገር መሆኗን ጠቅሰው፤ አምባሳደሯም በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙት እንዲጠናከር የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር የወዳጅ ሃገራት በተለይም የአሜሪካ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አንስተው ውይይት ማድረጋቸውም ነው የተገለጸው፡፡

አምባሳደር ሬድዋን በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ የህወሓት ቡድን ሲፈጥራቸው የነበሩ ችግሮችና በትግራይ ክልል የህግ የማስከበር እርምጃ የተወሰደበት ምክንያቶችን በዝርዝር ለአምባሳደሯ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

በተጨማሪ የሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽነት፣ ለመገናኛ ብዙኀን እንዲዘግቡ ሁኔታ መመቻቸቱን አብራርተዋል፡፡

አሁን መንግስት እያደረገ ካለው የ70 በመቶ ሰብዓዊ ድጋፍ በተጨማሪ ሌሎች በቂ ድጋፍ ሳያደርጉ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የሚሰጡት መግለጫ ተገቢነት እንደሌለውም አምባሳደር ሬድዋን ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.