Fana: At a Speed of Life!

አዳማ ከተማ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ ባስቆጠራት ግብ ከወልቂጤ ጋር ነጥብ ተጋርቷል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ ከአዳማ ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

1 ለ 0 ሲመሩ የነበሩት ወልቂጤ ከተማዎች በ90ኛው ደቂቃ ላይ በተቆጠረባቸው ግብ ከአዳማ ከተማ ጋር ነጥብ ተጋርተዋል።

ወልቂጤ ከተማዎች በረመዳን የሱፍ ግብ እረፍት ከመውጣታቸው በፊት 45ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠሩት ግብ ቀዳሚ መሆን ችለው ነበር።

አብዛኛው የጨዋታው ጊዜ በወልቂጤ ከተማ መሪነት ቀጥሎ የነበረ ቢሆንም በላይ ዓባይነት በ90ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ግብ አዳማ ከተማዎች አንድ ነጥብ ይዘው መውጣት ችለዋል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.