Fana: At a Speed of Life!

አዳዲስ ፈጠራን እና ዘመኑ የሚጠይቀውን የተወዳዳሪነት መስፈርት ማሟላት የሚችል ትውልድ ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል-አቶ ታንኳይ ጆክ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዳዲስ ፈጠራን እና ዘመኑ የሚጠይቀውን የተወዳዳሪነትን መስፈርት ማሟላት የሚችል ትውልድ ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ታንኳይ ጆክ አስታወቁ፡፡
አቶ ታንኳይ ጆክ ይህንን የተናገሩት በክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጅ አዘጋጅነት በአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ዙሪያ ከሴክተር መስሪያ ቤቱ ለተውጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በተሰጠበት ወቅት ነው።
በወቅቱም ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ታንኳይ ጆክ÷ የልማት ሃይል የሆነውን ወጣት በቀለም ትምህርት ያገኙውን እውቀት አዲስ ፈጠራ ከሳይንስ እና ከዘመኑ ቴክኖሎጂ አጣምሮ እንዲሄድ ማድረግ ካልተቻለ ዘመኑ የሚጠይቀውን ተወዳዳሪ ትውልድ ማፍራት እንደማይቻል ገልጸዋል።
ፈጠራን ከማበረታታት ጎን ለጎን በፈጠራ የተገኙትን አዕምሯዊ ንብረቶችን ጥበቃ ማድረግ ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም አዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ጋር በተያያዘ አንዱ የንግድ ምልክት፣ የባለቤትነት ፈቃድ፣ የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች እሴቶች በልማት ዙሪያ ግንዛቤ ለማዳበር በመሆኑ የሚጠበቅባቸሁን ሃላፊነት እንድትወጡ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤርሚያስ የማነ ብርሃን በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ማግኘትት ያለባትን ተወዳዳሪነት እያገኘች አለመሆኑን በመጥቀስ ማህበረሰቡ ስለ አዕምሯዊ ንብረት ያለው ግንዛቤ ማነስ ምክንያት ነው ማለታቸውን ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.