Fana: At a Speed of Life!

አገርን ከጥፋት ለመታደግ መዘጋጀታቸውን የብርሸለቆ ምልምል ሰልጣኞች አስታወቁ

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ዕዝ ሙዚቃ እና ቴአትር ቡድን በብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ35ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች የመድረክ ስራዎችን አቅርቧል፡፡

የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዘዥ ኮሎኔል ጌታቸው አሊ ወደ ማዕከሉ በመምጣት የኪነ-ጥበብ ድግስ ላዘጋጁ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የምዕራብ ዕዝ ሙዚቃ እና ቴአትር ቡድን አስተባባሪ ሌተናል ኮሎኔል ጥላሁን በቀለ በበኩላቸው÷ ኪነ-ጥበብ በሰላም ጊዜ ለአገር እድገት ትልቅ ሚና እንዳለው ሁሉ በጦርነት ወቅት ወኔን፣ቆራጥነትን፣የስነ-ልቦና ዝግጁነትን የሚቀሰቅስ የጦር መሳሪያ በመሆኑ አገራችን ያጋጠማትን ወራሪ ሃይል ለመቀልበስ በተለያዩ ቦታዎች ቅስቀሳ በማድረግ የበኩላችንን ድርሻ እየተወጣን እንገኛለን ብለዋል::

ምልምል ሰልጣኞቹ የዕዙ ሙዚቃና ቴአትር ቡድን ሠራዊቱ ያለበት ቦታ ድረስ በመገኘት የተለያዩ ሞራል ቀስቃሽ የሆኑ ሃገራዊ ጣዕመ ዜማዎችን በማቅረባቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
የሚሰጣቸውን ወታደራዊ ስልጠና በድል በመወጣት አገርን ከጥፋት ሃይሎች ለማዳን ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.