Fana: At a Speed of Life!

አገር በምትፈልገው አውድ ሁሉ በግንባር መሰለፍ ያስፈልጋል – ከንቲባ አዳች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘላቂ ሰላምና ፀጥታዋ የተጠበቀ የበለፀገች አገርን ለማስቀጠል አገር በምትፈልገው አውድ ሁሉ በግምባር ቀደምትነት መሰለፍ እንደሚያስፈልግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

በኢትዮጵያ መፅሐፍ ቅዱስ ጥናት በተዘጋጀው መድረክ “ስለ ሀገራችን ሰላም ዕድገትና አንድነት በመተባበር እንስራ” በሚል የምክክር መድረክ ተካሄዷል።

ከንቲባዋ በዚህ ወቅት ሰላም የአገር መሰረት ነው፤ ይህ ከኢትዮጵያውያን የተደበቀ ሀቅ አይደለም፤ ለሰላም ዋጋ ሲሉ ኢትዮጵያውያን ብዙ መስዋዕነት ከፍለዋል ብለዋል።

ሰላምን በሚያውክ እብሪተኛ ስብስብ አገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟን አጥታለች፤ የሰላም ተባባሪ ጓደኛ ትፈልጋለች፤ እብሪተኞችንም ትጠላለች ሲሉ ገልፀዋል።

ዘላቂ ሰላምና ፀጥታዋ የተጠበቀ የበለፀገች አገርን ለማስቀጠል አገር በምትፈልገን አውድ ሁሉ በግምባር ቀደምትነት መሰለፍ ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

የምክክር መድረኩ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ የመለያየትና የግጭት ሂደቶች ተለውጠው ዘላቂ ሰላም በአገሪቱ ለማስፈን በሚያስችልበት ሁኔታ ለመምከር መዘጋጀታቸውን ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.