Fana: At a Speed of Life!

አገር በቀል እውቀቶችንና የግጭት መፍቻ እሴቶችን ለትውልድ ማስተማሪያ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣መስከረም 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ሀገር በቀል እውቀቶችንና የግጭት መፍቻ እሴቶችን ከዘመናዊ ትምህርት ጋር አስተሳስሮ ለትውልድ ማስተማሪያ ማድረግ እንደሚገባ የብሄራዊ እርቀ-ሰላም ኮሚሽን ገለጸ።
ከ320 በላይ አገርበቀል የእርቅ ዘዴዎችን ለጥናትና ምርምር ማዘጋጀቱም የተገለፀ ሲሆን÷የኮሚሽኑ አባል አያልነህ ሙላት፤ “የኢትዮጵያውያን ችግር በራሳቸው በኢትዮጵያን እንጂ በሌሎች አገሮች መፍትሔ ሊገኝለት አይችልም”ብለዋል።
ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ እንደመሆኗ በእያንዳንዱ አካባቢ ያለውን በጎ ልማድና ባህላዊ የእርቀ-ሰላም ዘዴ በሳይንሳዊ ዘዴ አስተሳስሮ መጠቀም ወቅቱን የዋጀ መፍትሔ ይሆናልም ነው ያሉት።
አገር በቀል እውቀቶችንና የግጭት መፍቻ እሴቶችን ከዘመናዊ ትምህርት ጋር አስተሳስሮ ለትውልድ ማስተማሪያ በማድረግ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ጠቁመዋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ግንዛቤ ማስጨበጫ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደበበ ሰይፉ፤ ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ዓላማ አኳያ ወቅታዊ ግጭቶች ሲፈጠሩ አፋጣኝ መፍትሄ የሚሰጥ አለመሆኑን አስረድተዋል።
በተለይም አገር በቀል የግጭት አፈታትና የእርቅ ዘዴዎችን በመጠቀም “ለኢትዮጵታዊያን የዘላቂ ሰላም መሰረት ለመጣል ኮሚሽኑ ይሰራል” ብለዋል።
በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች የግጭቶችን መነሻዎች በጥናት በመለየት ለጥናትና ምርምር ዝግጁ በማድረግ ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.