Fana: At a Speed of Life!

አገር አቀፍ የአምራች ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገር አቀፍ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ያዘጋጀው ኤግዚቢሽንና ባዛሩ “የአገራችንን ምርት በመጠቀም ነጋችንን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን ÷እስከ  ፊታችን ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚቆይም ተመላክቷል፡፡

መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት  የኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳሬክተር አቶ ብሩ ወልዴ÷ ተቋሙ ለአምራች ዘርፉ ምቹ የአሰራር ስርዓትን ለመፍጠር፣ የአገር በቀል አምራቾችን ቁጥር ለመጨመርና የነባሮችን የማምረት አቅም ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዘርፉን የፋይናንስ እጥረት ለመፍታት በተለያዩ ተቋማት ተደራሽ የሚደረግ የሊዝ ፋይናንስና የስራ ማስኬጃ ብድር ተመቻችቶ ሲሰራ መቆቱን ጠቁመው÷ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚፈልጉትን የፋይናንስ ፍላጎት ከማሟላት አንጻር በቂ ባለመሆኑ የተለየ የድጋፍ አሰራር በቀጣይ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

አምራች ኢንተርፕራይዞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን አቅም ማሳደግ እንደሚስፈልግ እና ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚጠይቅም ነው የገለጹት፡፡

በቀጣይ በጀት ዓመት ብቃት ያላቸውን ኢንተርፕራይዞች የመለየት፣ የመደገፍና የማዘጋጀት ስራ በመስራት በዓለም አቀፍ ገበያ እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

በኤግዚቢሽንና ባዛሩም ከ227 በላይ የሚሆኑ በጨርቃ ጨርቅ፣ በአልባሳትና ቆዳ ውጤቶች፣ በብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ እንዲሁም የኢንጅነሪንግ ስራዎች ተቋማት መሳተፋቸውን ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.