Fana: At a Speed of Life!

አገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው አገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ “ምርምር ቀጣይነት ላለው እድገት”በሚል መሪ ቃል በወራቤ ዩኒቨርሲቲ  እየተካሄደ ነው።

የምርምር ኮንፍረንስ መድረኩ  በምርምር ዙሪያ መምህራን አቅም እንዲያጎለብቱ ከነባር ተመራማሪዎች ልምድ እንዲለዋወጡ እንደሚያስችል ተመላክቷል።

ተመራማሪዎች የምርመር ስራዎቻቸውን በተለያየ ዓለም አቀፍ ጆርናል እንዲያሳትሙ ማብቃትን ያለመ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ላይ በከፍተኛ ተመራማሪዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የተሰሩ ከ40 በላይ የምርምር ስራዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ የምርምር ኮንፍረንስ ላይ ከ21 በላይ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተጋበዙ የስራ ሃላፊዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተሳትፈዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.