Fana: At a Speed of Life!

አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገነባውን የመንገድ ስራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎ በአርባ ምንጭ ከተማ በ500 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባዉን የዘጠኝ ኪሎ ሜትር የአስፖልት ኮንክሪት መንገድ ስራ ዛሬ አስጀመሩ።

አቶ ታገሠ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት የቱሪስት መዳረሻ የሆነችው የአርባ ምንጭ ከተማን የመሠረተ ልማት ችግር በመፍታት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ ይገባል።

የመንገዱ መገንባት የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችንና ሌሎችን በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል።

ግንባታውን በጥራትና በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ መንግስት የበኩሉን ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘዉዴ በበኩላቸው፥ ያረጁ መንገዶች የከተማውን መንገዶች የከተማውን ውበት ከማበላሸት ባለፈ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖው መቆየታቸውን ገልጸዋል።

የመንገዱ መገንባት የህዝቡን የልማት ጥያቄን ከመፍታትም በላይ የትራፊክ ፍሰትን የተሳለጠ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታው በ2 ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

500 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የሚገነባዉ የአርባ ምንጭ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ ግንባታ የጎርፍ መውረጃ ቦይ ሥራዎችንም ያካትታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.