Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ ለዓለም ሰላም መስፍን የድርሻዋን እየተወጣች  ነው- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በ986ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ጥበቃ ም/ቤት የበይነ መረብ ውይይት ተሳትፈዋል።
ውይይቱ በአፍሪካ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።
አቶ ደመቀ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷አፍሪካ ለዓለም ሰላም መስፈን የድርሻዋን እየተወጣች መሆኗን ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ አገራት በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ የህይወት መስዋዕትነት ለከፈሉ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችም ያላቸውን ክብር ገልጸዋል።
በዓለም ሰላምና ጸጥታ የማስፈን ዓላማ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የባለብዙ ወገን መድረኮች መመስረት በምክንያትነት እንደሚጠቀስ በንግግራቸው አውስተዋል።
የሰላም አስከባሪ ኃይል ያሰማሩ አገራት እስከሕይወት መስዕዋዕትነት ድረስ ዋጋ እየከፈሉ መሆኑን ገልጸዋል።
አያይዘውም ለሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች የሚመደበው የፋይናንስና የሎጀስቲክ አቅርቦት መቀነስ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ያስገደደ መሆኑንም አንስተዋል።
በአሁኑ ወቅትም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘም ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚስፈልግ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ጸጥታ ም/ቤት በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ካለው ተጨባጭ ተሞክሮ አኳያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ዙሪያ በሚወጡ ፖሊሲዎችና እቅዶች ወቅት ተሳታፊ ማድረግ ጠቃሚ እንደሆነም ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በተሻለ ብቃትና ቅልጥፈና ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች የተሳተፉ አገራት መካከል የተሻለ ቅንጅት ማድረግ ፣ ለአቅም ግንባታ ተግባራት ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ እንዲሁም በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ሴቶች ያላቸውን ልዩ ሚና በመጥቀስ ተሳትፏቸውን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ማከናወን እንደሚስፈለግ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨመረሻም የአፍሪካ ሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ያለባቸውን ተግዳሮቶችን ለመፍታት አፍሪካዊያን የጋራ አቋም በመያዝ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ በአጽንዖት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.