Fana: At a Speed of Life!

ኡጋንዳ በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ትምህርት ቤቶቿን ዘጋች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡጋንዳ የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ ትምህርት ቤቶቿን ዘግታለች፡፡
የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ በሀገሪቱ በሁለተኛው የኮቪድ -19 ማዕበል ብዙ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ በመሆኑ ትምህርት ቤቶችን የዘጉ ሲሆን ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ቦታዎችንም ከልክለዋል፡፡
በተጨማሪም የህዝብ ትራንስፖርት ከሐሙስ ጀምሮ ይታገዳል ነው የተባለው ፡፡
የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ ሲኒማ ቤቶች እና ቲያትር ቤቶችም ተዘግተዋል ፡፡
የትምህርት ቤቶችና የስብሰባዎች እግድም ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን ለ42 ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ እግድ ይፋ የሆነው የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር በአንድ ቀን 1 ሺህ 259 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ከገለጹ ከሰዓታት በኋላ ነው ተብሏል፡፡
በኡጋንዳ እስካሁን 52 ሺህ 929 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 374 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
.
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.