Fana: At a Speed of Life!

ኢሬቻን ለማክበር ከሀላባ ዞን ለተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች በምዕራብ አርሲ አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻን ለማክበር ከደቡብ ክልል ሀላባ ዞን የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ምዕራብ አርሲ ዞን ላይ አቀባበል ተደረገላቸው።
የዞኑ ማህበረሰብ ከሀላባ ተነስተው በሻላ ወረዳ አጄ ከተማ ሲደርሱ በሻሸመኔ እና በነጌሌ አርሲ ከተሞች የዞን አመራሮችና የከተማ ነዋሪዎቹ በተገኙበት አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
የሀላባ ህዝብ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር በደም የተሳሰረ ህዝብ መሆኑን የሀላባ ዞን አስተዳዳሪ ዶክተ ር መሀመድ ኑሪዬ በአቀባበሉ ላይ ተናግረዋል።
ኢሬቻ የኦሮሞ አንድነት የሚታይበትና ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑበት በመሆኑ እኛም እንደ ሀላባ ዞን ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ለማክበር ወደ ኢሬቻ እየተጓዝን እንገኛልም ብለዋል፡፡
የኢሬቻ በዓልን ለማክበር እንደ ዞኑ በቢሻን ጉራቻ፣ በዶዶላ፣ በሀደብ ሀሳሳና በሻላ መስመር ለተለያየ የማህበረሰብ ክፍል ደማቅ አቀባበል መደረጉን የቀድሞው የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አበራ ቡኖ ተናግረዋል።
የኢሬቻ በዓል የኦሮሞን አንድነት ከመፍጠር አልፎ ብሄር ቤረሰቦች ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ይበልጥ ያጠነክራልም ነው ያሉት አቶ አበራ፡፡
በጀማል ከድሮ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.