Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር ጉዳይ የጋራ መፍትሄ ለማበጀት የተፈራረሙት ስምምነት በሱዳን በኩል ተጥሷል- የድንበር ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር ጉዳይ የጋራ መፍትሄ ለማበጀት የተፈራረሙትን ስምምነት ሱዳን መጣሷን የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ኮሚሽን አባላት ገለጹ።

በኢትዮጵያ በኩል የተወከሉት የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ኮሚሽን አባላት በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።

የኮሚሽኑ አባል አምባሳደር ኢብራሂም እንድሪስ በመግለጫቸው ሁለቱ ሃገራት በፈረንጆቹ 1972 በድንበር ጉዳይ የጋራ መፍትሄ ለማበጀት የተፈራረሙትን ስምምነት ሱዳን መጣሷን አብራርተዋል።

በስምምነቱ መሰረት ሃገራቱ በድንበር ጉዳይ የጋራ መፍትሄ እስከሚያስቀምጡ ድረስ መሬት ላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ እንዲቀጥል ያስገድዳል።

ሆኖም ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ በመግባት የያዘችው መሬት ይህንን ስምምነት የሚጥስ መሆኑን አስረድተዋል።

የድንበር ጥሰቱ በግብርና ምርትና በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ዜጎችን ለመፈናቀል ዳርጓልም ብለዋል።

በመሆኑም ሃገራቱ ዓለም አቀፍ ህግንና የድንበር ስምምነትን በማክበር በሰላማዊ መንገድ በውይይት መፍታት ይኖርባቸዋል ማለታቸው ኢዜአ ዘግቧል።

ሱዳን በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ገብታ የያዘችውን መሬት በህግ የሚያስጠይቃት በመሆኑ በአስቸኳይ ለቃ ወደ ነባራዊ ሁኔታዋ መመለስና በ1972 የተደረሰውን ስምምነት እንድታከብርም ጠይቀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.