Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ የ32 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ የ32 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ያስሚን ዎሃብረቢ እና በኢትዮጵያ የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶንግ ሆ ኪም ተፈራርመውታል፡፡

ስምምነቱ በቀጣዮቹ አምስት አመታት ለሚተገበሩት የገጠር የግብርና ማሻሻያ፣ የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያና አካባቢያዊ ስነ ምህዳር ማገገሚያ እንዲሁም ለተፋሰስ ልማትና ለአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻ ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋምና አካባቢያዊ ስነ ምህዳር ማገገሚያ ፕሮግራም እንደሚተገበር ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሃገሪቱን አረንጓዴ ልማት በመደገፍ ተግባራዊ በሚደረግባቸው አካባቢዎች የሚገኙ 55 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም በገጠር ግብርና ማሻሻያ ፕሮግራሙ በአነስተኛ ግብርና ለተሰማሩ አርሶ አደሮችን እና የገጠር ግብርና የሽግግር ማዕከላትን ለመደገፍ የሚውል ይሆናል፡፡

ይህም በዘርፉ ያለውን የምርትና የገበያ ትስስር በማሳደግና በመደገፍ የአርሶ አደሮችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያስችላልም ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.