Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ512 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የብድርና ዕርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ መካከል የ512 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የብድርና ዕርዳታ ስምምነት ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴና የዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ዑስማን ዲዮን ተፈራርመውታል፡፡

በስምምነቱ መሰረት 312 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላሩ ዕርዳታ ሲሆን 200 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ ብድር ነው፡፡

ገንዘቡ በኢትዮጵያ እየተከናወነ የሚገኘውን የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር ለማጠናከርና ከዚህ ቀደም በመርሃ ግብሩ ያልተካተቱ ተጨማሪ ቦታዎችን ለማገዝ ይውላል ነው የተባለው፡፡

መርሃ ግብሩ በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚገኙ የገጠር አካባቢዎችን እና በድርቅ ምክንያት ለምግብ ዕጥረት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡

በዘመን በየነ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.