Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ለማዳከምና አንድነቷን ለማናጋት ከየትኛውም አካል የሚሰነዘር ትንኮሳ እና ጫና በአንድነት ልንመክት ይገባል -አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ለማዳከምና አንድነቷን ለማናጋት ከየትኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ አካል የሚሰነዘር ትንኮሳ እና ጫና በአንድነት ልንመክት ይገባል ሲሉ  አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ተናገሩ።

በተባበሩት መንግስታት የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ÷ ኢትዮጵያን ለማዳከምና አንድነቷን ለማናጋት ከየትኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ አካል የሚሰነዘር ትንኮሳ እና ጫና በአንድነት ልንመክት ይገባል ብለዋል፡፡

በአሜሪካ ኒውዮርክ፣ ኮኔክትከት እንዲሁም በሌሎች ስቴቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ  በዌብናር ውይይት ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  ቋሚ መልዕክተኛ ፅህፈት ቤት አማካኝነት ሲሆን÷ አላማውም በወቅታዊ ሁኔታና ምዕራባዊያን በኢትዮጵያ ላይ እያሳዩት ያለውን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት ማዕከል ያደረገ ነው ተብሏል::

በውይይቱ  የታላቁን የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ሂደት፣ እንዲሁም መጭው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫም ተዳሰዋል::

በውይይቱ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ተሳታፊዎቹን አወያይተዋል::

አምባሳደሩ በቅርቡ ምዕራባዊያን በሀገራች ላይ እያሳዩት ያለው ያልተገባ ጣልቃ ገብነት ምን ይዘት እንዳለው በተለይም  ሰሞኑን የአሜሪካ ሴኔት ያወጣውን ሪዞልሽን ምንነት፣ እንዲሁም በተመድ በፀጥታው ም/ቤት ይቀርቡ የነበሩትን ጉዳዮች በዝርዝር ካስረዱ በኋላ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከምና አንድነቷን ለማናጋት ከየትኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ አካል የሚሰነዘር ትንኮሳ እና ጫና በአንድነት ልንመክት ይገባል ብለዋል::

በተለይም በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚቀርቡትን የተሳሳቱ አመለካከቶች እና እንቅስቃሴዎች መመከት ያስፈልጋል ያሉት አምባሳደር ታዬ÷ ባለንበት አካባቢ የሚገኙ ተፅእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን፣ የፓርላማ አባላትንና የሚዲያ ተቋማትን አግኝቶ እውነታውን ማስረዳት ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን በማስገንዘብ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያን ለማዳከምና አንድነቷን ለማናጋት ከየትኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ አካል የሚሰነዘር ትንኮሳ እና ጫና ተገቢ እንዳልሆነና ለመመከት እንደሚሰሩ፣  የታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርጉና በየአካባቢያቸው የሚገኙ የስቴት እና የፌደራል ባለስልጣናትን፣ የኮንግረስ አባላትን እና ሴናተሮችን በማነጋገርና የጽሁፍ መልዕክቶችን በመላክ በኢትዮጵያ ያለውን ትክክለኛ ገፅታ እንዲገነዘቡ እንደሚያደርጉመግለጣቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.