ኢትዮጵያን ለነገው ትውልድ ስናስረክብ ምቹ የመኖሪያ አካባቢን በመፍጠር መሆን አለበት- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ለነገው ትውልድ ስናስረክብ ምቹ የመኖሪያ አካባቢን በመፍጠር ጭምር መሆን አለበት ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት÷ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በተገኙበት የአካባቢ ማስዋብ ፕሮጀክት የምረቃ ሥነ-ስርዓት አካሂዷል፡፡
በስነ-ስርዓቱ ላይ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አንደገለጹት÷ አካባቢን ለኑሮና ለስራ ምቹ ማድረግ ሁሉም ዜጋ ባህል ሊያደርገው ይገባል።
ጋምቤላን በማጽዳት ለኑሮ ምቹ እና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ሁሉም መረባረብ እንዳለበት ጠቁመው÷ የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ተቋም የጀመረውን አካባቢን የማስዋብ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ለርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ሰርቶ ማስረከቡን ገልጸዋል።
በቀጣይም ሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች አካባቢን የማስዋብ ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበው÷ በስራው አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፒተር ሆው በበኩላቸው÷ አገራችን በአረንጓዴ ልማት ለአፍሪካና ለመላው ዓለም አርአያ በመሆን የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነች ነው ብለዋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ተጋበዥ እንግዶች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!