Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያስተሳስረው የሀዋሳ ሞያሌ መንገድና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክት ዛሬ ይመረቃል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያስተሳስረው የሞምባሳ-ናይሮቢ -አዲስ አበባ- ኮሪደር ግንባታ አካል የሆነው የሀዋሳ ሞያሌ መንገድ እና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ይመረቃል።

የሞንባሳ ናይሮቢ አዲስ አበባ ኮሪደር ግንባታ አካል የሆነው እና የ500 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሃዋሳ  ሞያሌ መንገድ እና የሞያሌ የጋራ  የፍተሻ ጣቢያ ነው የሚመረቀው።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ እንደተናገሩት፥ ዛሬ የሚመረቀው መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጭ የተደረገበት ነው።

ወጪው በአፍሪካ ልማት ባንክ የረጅም ጊዜ የብድር ድጋፍ የተሸፈነ መሆኑንም አስታውቀዋል።

መንገዱ በመስመሩ ለሚገኙ ከተሞች የእርሻ እና የኢንደስትሪ ዞኖች እና የቱሪስት መዳረሻወች በዘመናዊ መንገድ ከማስተሳሰሩ ባለፈ የኢትዮጲያ እና የኬኒያ መንግስት የሁለትዬሽ የንግድ ልውውጥ ግንኙነትን እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።

በምረቃ ስነ ስርአቱ የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በምንይችል አዘዘው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.