Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ወደ ሰላም ለመመለስ እየታገሉ መሆናቸውን የጋሽና ግንባር ዘማቾች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት ቡድን በደቡብ ጎንደር ዞን ወረራ ፈጽሞ የወገን ጦር ባደረሰበት ከፍተኛ ኪሳራ ቢባረረም እንደገና በዞኑ ስልቱን ቀይሮ ለመግባት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ፍጹም አይሳካለትም ሲሉ በጋሸና ግንባር ያሉ ዘማቾች ተናገሩ፡፡
ጠላት ከሰሞኑ በዳውንት መስመር ወደ ታች ጋይንት ለመግባት ያደረገው ሙከራ በአገር መከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ በፋኖ፣ በሚሊሻ እና በሕዝባዊ ሠራዊት ከባድ ጥቃት ደርሶበት ከሽፏል።
የዞኑ ሕዝብ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ በአጎራባች የሰሜን ወሎ ዞን ወረዳ ጭምር እየተፋለመ እንደሚገኝ የታች ጋይንት ወረዳ አስተዳዳሪ አጣናው ደሳለኝ ገልጸዋል።
በጋይንት – ጋሸና ግንባር ድጋፍ እየሰጡ ያሉት ዶክተር ሣለ አያሌው የወገን እንቅስቃሴ የተናበበ እና በአጭር ጊዜ የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ተናግረዋል።
ህብረተሰቡም የጠላትን አስከፊነት ተገንዝቦ እየመከተ እንደሆነ ጠቁመው÷ ከሌሎች ግንባሮች ጋር በተናበበ እና በተቀናጀ አግባብ ጠላትን ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት እየተሠራ ነው ብለዋል።
ሁሉም የደቡብ ጎንደር ዞን ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ምግብ ከማቅረብ ጀምሮ ምሽግ ድረስ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረጉ ነውም ተብሏል፡፡
የአሸባሪውን ወራሪ ቡድን እኩይ ተግባር ለመቀልበስ ጠላት በተሰለፈበት ልክ መንቀሳቀስ ብቻ ሳይሆን÷ በላቀ በሳል አመራር የተወረሩ አካባቢዎችን በአጭር ጊዜ ነጻ አውጥቶ ሕዝቡን መታደግ እና ሀገሪቱን ወደ ሰላም መመለስ እንደሚገባ መገለጹን አሚኮ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.