Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊቷ ሎዛ አበራ በአውሮፓ ሁለተኛ የሊግ ዋንጫ ድሏን አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ሎዛ አበራ በአውሮፓ ሁለተኛ የሊግ ዋንጫ ድሏን ማሳካት ችላለች።

የቀድሞዋ የአዳማ ከተማ ተጫዋች ከዚህ ቀደም በስዊድን የሴቶች ሊግ ከኩንግስባካ ክለብ ጋር የስዊድን የሴቶች የእግር ኳስ ውድድርን በፈረንጆቹ 2018 ማሸነፍ ችላ ነበር።

በወቅቱ ለክለቡ ስምንት ጨዋታዎችን አድርጋ ሶስት ጎሎችን አስቆጥራለች።

ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላም ወደ ቀድሞ ክለቧ አዳማ ከተማ በመመለስ ክለቡ የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግን ለመጀመሪያ ጊዜ አሸናፊ እንዲሆን የበኩሏን ሚና ተወጥታለች።

በወድድሩ አጋማሽ ላይ በመምጣትም 18 ጎሎችን በማስቆጠር ለአራተኛ ጊዜ ሊጉን በኮኮብ ጎል አግቢነት መጨረስ ችላለች።

ሎዛ ከአዳማ ቆይታዋ በኋላ ወደ ማልታው ቢርኪርካራ ክለብ በመዛወርና 30 ጎሎችን ማስቆጠር የሊጉ ኮከብ ጎል አግቢ ሆና አጠናቃለች።

ከዚህ ባለፈም በአውሮፓ ቆይታዋ ሁለተኛ የሊግ ዋንጫዋን ከክለቧ ጋር ማሳካት መቻሏን የጎል ዶት ኮም ዘገባ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.