Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊያን በያሉበት ሆነው በዛሬው ዕለት ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ያላቸውን ድጋፍ አሰሙ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊያን በያሉበት ሆነው በአሁኑ ሰዓት ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ያላቸውን ድጋፍ አሰሙ።
 
ድምፃቺን ለግድባችን በሚል መሪ ቃል በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያን ለግድቡ ያላቸውን ድጋፍ ነው ያሰሙት።
 
የዚሁ አካል የሆነ መርሃ ግብርም በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በስነ ስዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
 
እንዲሁም አርቲስቶች ፣ ምሁራን ፣ ፓለቲከኞች ፣ የሀይማኖት መሪዎች እና የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
 
ተሳታፊዎቹም በተለያዩ መንገዶች ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ያላቸውን ድጋፍ አሰምቷል።
 
በአዲስ አበባ ጎዳናዎችም ህብረተሰቡ ደስታቸውን ገልፀዋል።
 
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ተሸከርካሪዎች የኢትዮጰያን ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብና ክላክስ በማሰማት ነው ን ደስታቸውን የገለፁት።
 
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና ሊፍት ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ያዘጋጁት ይህ መርሃ ግብር ኢትዮጵያን የህዳሴ ግድብ ለደረሰበት ደረጃ ምስጋና ለማቅረብ ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.