Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የአመራርነት ቦታ እንዲይዙ ብዙ መሠራት  አለበት- ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የአመራር ቦታ እንዲይዙ ብዙ መሠራት አለበት ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቷ አዲስ የተሾሙትን የአፍሪካ ሕብረት ልማት ድርጅት- አውዳ-ኔፓድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናርዶስ በቀለ ቶማስ ጋር ተወያይተዋል።

ስራ አስፈጻሚዋ ናርዶስ ለዚህ ከፍተኛ ኃላፊነት በመብቃታቸውና የመጀመሪያ ሴት አመራር በመሆናቸው እንደ አገር የተሰማቸውን ኩራትና ደስታ ጠቅሰው÷ ያለንበት ወቅት በርካታ ፈተናዎችና ቀውሶች ያሉበት በመሆኑ ድርጅቱ ሚናውን እንዲወጣ ተገቢውን አመራር እንደሚሰጡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የአመራር ቦታ እንዲይዙ ብዙ መሠራት  አለበትም ብለዋል።

አውዳ-ኔፓድ 55 አገራትን የያዘ በዓለም ላይ ብቸኛ የልማት ድርጅት መሆኑን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአውዳ-ኔፓድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ናርዶስ በቀለ ባለፈው ጥር ወር በአዲስ አበባ በተካሄደው የሕብረቱ ጉባኤ መሾማቸው ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.