Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለራሷ ችግር መላ አታጣም- በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ10 ዓመታት በላይ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)ን በበላይነት የመራችው ኢትዮጵያ ለራሷ ችግር መላ አታጣም  ሲሉ በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒ ሞርጋን ተናገሩ።

አምባሳደር ጀምስ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና የቀጣናው ሀገራት ሁኔታን በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸውም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ተስፋ የሚጣልባትና ለዚህም ተግታ ስትሰራ የቆየች አገር ናት ብለዋል።

ቀጣናው በርካታ ውስብስብ ችግሮች ያሉበትና ብዙ የመልማት ፍላጎትና እድል ያለው አካባቢ ነው  ያሉት አምባሳደሩ፤ ይህን በመሰለ ክፍለ አህጉር ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ጠንካራ ሀገራት ቀጣናውን የማስተሳሰር ሚናቸው ትልቅ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ የውስጥ አንድነቷን ከማስጠበቅ አልፋ ለቀጣናዊ ትስስር አብርክቶዋን ማጠናከር አለባት ብለዋል አምባሳደር ጀምስ።

አምባሳደሩ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትም ይሁኑ ሌሎች አካላት ኢትዮጵያ ላለችበት ሁኔታ መፍትሄ እንድትሰጥ እድል መስጠት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በዚሁ መሰረት ጎረቤት ሀገራት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተዋናዮች ከመንግስት ጋር በቅርበት እንዲሰሩ የሰላም ጥሪ ማቅረብ አለባቸው ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ጥንታዊት እንደመሆኗ የውስጥ ችግሮቿን የምትፈታበት የዳበረ ልምድ ያላት ሀገር መሆኗን በመመስከር፤ በዚህ ወቅም የገጠማትን ጉዳይ በአግባቡ መወጣት እንደምትችል ሙሉ እምነት እንዳለቸውም ጨምረው ገልጸዋል።

አምባሳደር ጀምስ ኢትዮጵያ ከኮሪያ ጦርነት ጀምሮ ለዓለም ሰላም ዘብ ስትቆም መቆየቷንም አስታውሰዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.