Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ህዝብ 15 ቶን ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል የሚውል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ህዝብ 15 ቶን የሚያወጣ ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እና ሌሎች በሽታዎች መከላከል የሚውል ድጋፍ አደረገች።

ግማሽ ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣው ይህ ድጋፍ የህክምና ቁሳቁስና መድኃኒቶችን ያካተተ ነው።

ድጋፉንም የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በሞቃድሾ በመገኘት አበርክተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ድጋፉ ኢትዮጵያ በችግርም በፀጋም ከጎረቤቶቿ ጋር ተባብራ በመጓዝ ረገድ ያላት ጠንካራ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መገለጫ መሆኑን በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።

ይህም የህዝቦቿ ተካፍሎ የመብላትና ተጋግዞ የመኖር የቆየ እሴት ነፀብራቅ መሆኑንም ነው ያመለከቱት።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴና አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን ያካተተው የልዑካን ቡድኑ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ ፎርማጆ ጋር በሁለቱ ሀገሮች ሁሉን አቀፍ ትብብር ዙሪያ መምከሩንም አምባሳደር ሬድዋን አክለው ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የህክምና ቁሳቁስ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን መለገሷ ይተወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.