Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና እና ደቡብ አፍሪካ ጋር ተደልድላለች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድል ተጋጣሚዎች ተለይተዋል።

የማጣሪያ የምድብ ድልድሉ ትናንት ይፋ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ በምድብ 7 ተደልድላለች።

በምድቡ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ የኢትዮጵያ ተጋጣሚዎች ሆነዋል።

በማጣሪያው የየምድቦቹ አሸናፊዎች በዕጣ ድልድል እርስ በርስ በሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ አሸናፊ የሆኑ 5 ሃገራት በኳታሩ የዓለም ዋንጫ አፍሪካን ይወክላሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.