Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለዓለምና ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች -ዶ/ር አብርሃም በላይ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለዓለምና ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ፡፡

ዶክተር አብርሃም በቻይና አዘጋጅነት በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ የሚኒስትሮች የሰላምና የፀጥታ ፎረም ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ሚኒስትሩ በፎረሙ ባስተላለፉት መልዕክት÷ወቅቱ በዓለማችን ሆነ በአካባቢያችን የሚታዩ የጸጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሰላም ሃይሎች ጋር በትብብር መስራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡

የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያም በፓን-አፍሪካን መንፈስ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካውያን ለመፍታት እንዲቻል በጽናት እየሰራች መሆኗን አስረድተዋል፡፡

ዶ/ር አብርሃም የቻይና ህዝባዊ ሪፐብሊክ መንግስት አካታችና ሚዛናዊ አካሄድን በመከተል ለዓለም ሰላምና መረጋጋት እያደረገ ላለው ሚና ያላቸውን ክብርና አድናቆት መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

“የጋራ ደህንነትን ለማረጋገጥ አብሮነትና ቅንጅትን ማጠናከር ይገባል” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው 2ኛው የቻይና-አፍሪካ የሚኒስትሮች የሰላምና የፀጥታ ፎረም ከ50 በላይ ሚኒስትሮችና የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.