Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለጅቡቲ 40ሺህ ችግኞችን ላከች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በአገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በሃገር ውስጥ ብቻ ተገድቦ እንዳይቀርና ለጎረቤት አገራት ችግኝ ለማቅረብ ከተያዘው እቅድ አንዱ የሆነው ለጅቡቲ የተዘጋጀው 40 ሺህ ችግኝ ዛሬ ተልኳል።
በችግኝ ሽኝቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ሁኔታው ከጎረቤት አገር ጅቡቲ ጋር ከኢኮኖሚያዊ ትስስር ባለፈ ኢትዮጵያ ያላትን በጋራ የመልማት ፍላጎትን ያንፀባርቃል ብለዋል።
የኢትዮጵያና ጅቡቲ ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረነው ያሉት ከንቲባው፥ ድሬደዋ ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሳለጥ የአንበሳውን ድርሻ በመወጣት ላይ ትገኛለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው ክረምት 2 መቶ ሺህ ችግኞችን ለጅቡቲ ለመስጠት በያዘችው ዕቅድ መሠረትም 40 ሺው በአስተዳደሩ ተዘጋጅቶ መሠጠቱን ገልፀዋል።
ሀገራቱ በጋራ በመሆን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመቀናጀት እየሰሯቸው ያሉት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ከድር ጁሃር አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ በክረምቱ ለመትከል ካዘጋጀቻቸው 7 ቢሊየን ችግኞች ውስጥ አንድ ቢሊየኑ ለውጪ ሀገራት የሚሰጡ መሆናቸው በመድረኩ ተገልጿል።
ድሬዳዋና ጅቡቲ ተመሳሳይ የአየር ንብረት እንደመጋራታቸው፥ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በጋራ ለመስራት ያስችላቸዋል ያሉት ደግሞ በአስተዳደሩ የዱርና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የደን ልማትና እንክብካቤ ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ይመር ናቸው።
በነጌሶ ከድር
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.