Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኤምባሲዋን እንደገና ለመክፈት ማቀዷን ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ  ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኤምባሲዋን በቅርቡ እንደገና  ለመክፈት ማቀዷን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቷ ይህንን ያስታወቁት  ከሀገሪቱ  ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ጋር በኪንሻሳ ብሄራዊ ቤተመንግስት ከተወያዩ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ አያይዘውም የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት የሊቀመንበርነት ስፍራን ለሚረከቡት የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ተልእኳቸው የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልፀዋል፡፡

ሁለቱ ፕሬዚዳንቶችም በኪንሻሳ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለውን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከመወያየታቸውም ባለፈ  በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳቦችን ተለዋውጠዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለ-ወርቅ የታንዛኒያ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መጓዛቸው ይታወሳል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.