Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን ሲያሸንፍ አቡበክር ናስር ሐት-ትሪክ ሰርቷል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን ረፋድ 4፡00 ሰዓት ላይ በባህርዳር ስታዲየም ነው ያካሄዱት፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን ሦስት ግቦች አቡበከር ናስር ሲያስቆጥር፣ ታፈሰ ሰለሞን ደግሞ አራተኛዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡

ይህን ተከትሎም አቡበክር ናስር ሐት ትሪክ ሰርቷል፡፡

ሊጉን ፋሲል ከነማ በ28 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ ቡና በ24 ቅዱስ ጊዮርጊስ በ21 ይከተላሉ፡፡

በከሰዓቱ መርሃ ግብር ወልቂጤ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.