Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ቡና የስነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ አራት ተጫዋቾች ላይ ቅጣት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ስኬታማ የውድድር ዘመን እያሳለፈ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ የስነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ አራት ተጫዋቾች ላይ ቅጣት አስተላለፈ።

ታፈሰ ሠለሞን ፣ሚኪያስ መኮንን ፣ አዲስ ፍስሃ እና ሀይሌ ገ/ተንሳይ ድሬዳዋ የክለቡ ተጨዋቾች ከሚያድሩበት ሆቴል በመውጣት ባልተገባ መልኩ አልባሌ ቦታ በማሳለፋቸው የደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ብሏል፡፡

ቅጣት የተላለባፋቸው ተጫዋቾች በተለይ በኮቪድ19 ምክንያት ክለቦችም ሆኑ ፕሪሚየር ሊጉ በሚታመስበት በዚህ ወቅት ልዩ ጥንቃቄና ትኩረት ማድረግ ሲገባቸው ይህን አለመፈጸማቸውንም በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል።

በክለቡ ውስጥ የሚከሰቱ የስነ ምግባር ጥሰቶች በምክርና በተግሳፅ እየታለፉ የነበሩ ቢሆንም አንዳንዶቹን ለሌሎች መማሪያ በሚሆን መልኩ መቅጣት ተገቢ መሆኑንም ጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.