Fana: At a Speed of Life!

“ኢትዮጵያ ትጣራለች” በሚል መርሃ ግብር 160 ሚሊየን ብር ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ በተካሄደው “ኢትዮጵያ ትጣራለች” የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ 160 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል።
በዚህ ወቅትም ባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይተነው 50 ሚሊየን ብር፣ ጎመጁ ኦይል ኢትዮጵያ 20 ሚሊየን ብር፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 5 ሚሊየን ብር፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 2 ነጥብ 25 ሚሊየን ብር፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 3 ሚሊየን ብር፣ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ 1 ሚሊየን ብር፣ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ 1 ሚሊዮየ ብር ለመለገስ ቃል ገብተዋል።
በመርሃ ግብሩ በርካታ ግለሰቦች፣ ተቋማት እና ድርጅቶችም በርካታ ገንዘብ ለመለገስ ቃል ገብተዋል።
ከገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የተገኘው ገቢ ለመከላከያ ሠራዊቱ፣ ለአማራ ልዩ ሃይል፣ ለሌሎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች እንደሚውል አሚኮ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.